1 ሳሙኤል 10:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ ማድረግ የሚገባህን ሁሉ አድርግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም ምልክቶች በደረሱህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ የምትችለውን ሁሉ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም ምልክቶች በደረሱህ ጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ የምታገኘውን ሁሉ አድርግ። |
ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፣ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው፤ ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና።
በሕይወት በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበርሁ ሁሉ ከአንተም ጋራ እሆናለሁ፤ ከቶ አልጥልህም፤ አልተውህም።
ነገር ግን አባቴ ክፉ አስቦብህ፣ ይህን ሳላሳውቅህ ብቀርና በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ፣ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ፤ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋራ እንደ ነበር እንደዚሁ ከአንተም ጋራ ይሁን።