1 ሳሙኤል 10:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተም ጕዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው እስከ ትልቁ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፣ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፣ ሌላው ሦስት ዳቦ፣ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቍማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተም ጉዞህን በመቀጠል በታቦር እስካለው ባሉጥ ዛፍ ድረስ ትሄዳለህ፤ እዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ግልገል፥ ሌላው ሦስት ዳቦ፥ ሌላው ደግሞ የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም አልፈህ በታቦር ወደሚገኘው ወደ አንድ ትልቅ ዛፍ ትደርሳለህ፤ እዚያም ወደ ቤትኤል ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ ሦስት ሰዎችን ታገኛለህ፤ ከእነርሱ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶችን እየሳበ የሚሄድ ሲሆን ሁለተኛው ሰው ሦስት ኅብስት የተሸከመ ነው፤ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ የተሸከመ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ደግሞ አልፈህ፥ ወደ ትልቁ የታቦር ዛፍ ትደርሳለህ፤ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች ሲነዳ፥ ሁለተኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ደግሞ ወደ ፊት ትሄዳለህ፥ ወደ ታቦር ወደ ትልቁ ዛፍ ትደርሳለህ፥ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች፥ ሁለተኛው ሦስት ዳቦ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል፥ |
እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።
“እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ፣ የአጎቴ ልጅ አናምኤል ወደ ዘብ ጠባቂዎቹ አደባባይ መጥቶ፣ ‘የመቤዠቱን ርስት የማድረጉ መብት የአንተ ስለ ሆነ፣ በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን መሬቴን ለራስህ እንዲሆን ግዛው’ አለኝ።” ይህም የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወቅሁ፤
ከዚህም ጋራ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን ሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ለእህል ቍርባን፣ አንድ አራተኛ የሂን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን አቅርቡ።
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመግጠም እንደ ገና እንውጣን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ውጡና ግጠሟቸው” ብሎ መለሰላቸው።
ዲቦራ፣ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺሕ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤
ዛብሄልና ስልማናንም፣ “በታቦር ላይ የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ሁሉም እንዲህ እንደ አንተ ያሉ የንጉሥ ልጆች የሚመስሉ ናቸው” አሉት።