አዛሄልም፣ “ጌታዬ የሚያለቅሰው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕም መልሶ፣ “በእስራኤላውያን ላይ የምታደርሰውን ጕዳት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ጕልማሶቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናታቸውን በምድር ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ ያረገዙ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትቀድዳለህ” አለው።
1 ሳሙኤል 1:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏ ሕልቃናም እርሷን፣ “ሐና ሆይ፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሏ ሕልቃናም እርሷን፥ “ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ ባልዋ ሕልቃና “ሐና ሆይ! ስለምን ታለቅሻለሽ? ስለምንስ አትመገቢም? ስለምንስ ዘወትር ይህን ያኽል ታዝኚአለሽ? ከዐሥር ልጆች ይልቅ እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋ ሕልቃናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እርስዋም፥ “ጌታዬ እነሆኝ” አለችው። እርሱም፥ “ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከዐሥር ልጆች አልሻልሽምን?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም ሕልቃና፦ ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት። |
አዛሄልም፣ “ጌታዬ የሚያለቅሰው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕም መልሶ፣ “በእስራኤላውያን ላይ የምታደርሰውን ጕዳት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ጕልማሶቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናታቸውን በምድር ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ ያረገዙ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትቀድዳለህ” አለው።
“አንቺ መካን፣ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፣ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።
እርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልቱ ቦታ ጠባቂ መስሏት፣ “ጌታዬ፤ አንተ ወስደኸው ከሆነ፣ እባክህ እንድወስደው፣ የት እንዳኖርኸው ንገረኝ” አለችው።
ይህም በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ ሐና ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ታበሳጫት ነበር።