1 ቆሮንቶስ 4:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን፣ ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሰው ሁሉ መጨረሻ ያሰለፈን ይመስለኛል፤ ለዓለም ሁሉ፣ ለመላእክትም ለሰዎችም ትርኢት ሆነናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም ትንግርት ሆነናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔስ ለሞት ዝግጁዎች እንደ መሆናችን እኛን ሐዋርያቱን እግዚአብሔር የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል፤ እኛ ለሰዎችም፥ ለአለቆችም፥ ለዓለምም መዘባበቻ ሆነናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና። |
ወዲያውም በከተማው ሁሉ ሁከት ተነሣ፤ ሕዝቡም አንድ ላይ በማበር የመቄዶንያ ተወላጅ የሆኑትንና ከጳውሎስ ጋራ ይጓዙ የነበሩትን ጓደኞቹን፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ እየሮጡ ገቡ።
የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? አእምሮውን እንደ ጣለ ሰው ልናገርና እኔ እበልጣቸዋለሁ፤ ደግሞም ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት ተቃርቤአለሁ።
አንዳንድ ጊዜ በአደባባይ ለስድብና ለስደት ተጋልጣችሁ ነበር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ያለ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋራ ዐብራችሁ መከራን ተቀብላችኋል።