ሶፎንያስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ዳር ያለው ምድራችሁ የከብት ማሰማሪያ፥ የእረኞች መኖሪያና የመንጋዎች ማደሪያ በረት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩ ዳር ያለው ምድር፣ የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባሕሩም ዳር የግጦሽ መሬት፥ የእረኞች መስክና የበጎች በረት ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል። |
ቀድሞ በዶማ ተቈፍረው እህል ይበቅልባቸው የነበሩ ኰረብቶች ሁሉ ኲርንችትንና እሾኽን በመፍራት ማንም ወደዚያ አይሄድም፤ ነገር ግን የከብትና የበግ መንጋ መሰማሪያ ብቻ ይሆናሉ።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝብም ሆነ እንስሳ የማይኖርባት ምድረ በዳ በሆነች በዚህች ምድር እንደገና እረኞች የበጎቻቸውን መንጋ የሚያሠማሩበት መስክ ይኖራል።
የራባን ከተማ የግመሎች ማሰማርያ፥ መላውንም የዐሞን አገር የበጎች መዋያ አደርገዋለሁ፤ በዚህም ዐይነት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።