እግዚአብሔርም፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በስተ ሰሜን በኩል ተመልከት!” አለኝ፤ በተመለከትኩም ጊዜ በቅጽር በሩ ፊት ለፊት ባለው መሠዊያ አጠገብ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስ ምስል ነበር።
ዘካርያስ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም እንደገና ወደ እኔ መጥቶ “የሚመጣው ነገር ምን እንደ ሆነ ተመልከት!” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደ ሆነ እይ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ “ዐይኖችህን አንሣ፥ ይህችም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ” አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወጥቶ፦ ዓይኖችህን አንሣ፥ ይህችንም የምትወጣው ምን እንደ ሆነች እይ አለኝ። |
እግዚአብሔርም፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በስተ ሰሜን በኩል ተመልከት!” አለኝ፤ በተመለከትኩም ጊዜ በቅጽር በሩ ፊት ለፊት ባለው መሠዊያ አጠገብ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስ ምስል ነበር።
ስለዚህም መልአኩ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ቃል እንዲህ ብለህ ዐውጅ አለኝ፥ “እኔ ለተቀደሰችው ከተማዬ ለኢየሩሳሌም ታላቅ ፍቅርና ብርቱ ቅናት አለኝ፤
ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ “እነዚህ ቀንዶች የምን ምሳሌ እንደ ሆኑ ንገረኝ” አልኩት። እርሱም “እነርሱ የይሁዳ፥ የእስራኤልና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች እንዲበተኑ ያደረጉ መንግሥታት ናቸው” አለኝ።
እኔም “ጌታዬ ሆይ! እነዚህ ፈረሶች የምን ምሳሌ ናቸው?” ብዬ ጠየቅሁት። እርሱም “የእነዚህ ፈረሶች ምሳሌነት ምን እንደ ሆነ አሳይሃለሁ፤