Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ “እነዚህ ቀንዶች የምን ምሳሌ እንደ ሆኑ ንገረኝ” አልኩት። እርሱም “እነርሱ የይሁዳ፥ የእስራኤልና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች እንዲበተኑ ያደረጉ መንግሥታት ናቸው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም፦ እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም፦ እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 1:19
20 Referencias Cruzadas  

ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ” አለው።


የይሁዳና የብንያም ሕዝብ ጠላቶች የሆኑ ነዋሪዎች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሰሙ።


ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ነዋሪዎች የሆኑት ሕዝቦች አይሁድን በማስፈራራትና ተስፋ ለማስቈረጥ በመሞከር ቤተ መቅደሱን እንዳይሠሩ ሊከለክሉአቸው ተነሣሡ።


አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በተነሣበትም ዘመን፥ እንደገና ቢሽላም፥ ሚትረዳት፥ ጣብኤልና ሌሎቹ የእነርሱ ግብረ አበሮች የክስ ደብዳቤ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ጻፉባቸው፤ ይህም ደብዳቤ የተጻፈው በሶርያ ፊደልና ቋንቋ ሲሆን ተተርጒሞ በንባብ እንዲሰማ የተላከ ነበር።


በዚያን ጊዜ የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ የነበረው ታተናይና ሽታርቦዝናይ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ባለሥልጣኖች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፦ “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራትና ቅጽሩንም ለማደስ ማን ፈቀደላችሁ?” ሲሉ ጠየቁአቸው።


ትዕቢተኞችን ‘አትታበዩ’ ክፉዎችን ‘አታምፁ’ እላቸዋለሁ፤


በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ ወይም በትዕቢት አትናገር።”


የሞአብ መከላከያ ኀይል ተሰብሮአል፤ ሥልጣንዋም ተገፎአል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ቀጭን ሐር ለብሶ ከወንዝ በላይ በኩል የቆመው መልአክ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ በዘለዓለማዊው አምላክ ስም በመማል “ሦስት ዓመት ተኩል ይወስዳል፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚደርሰው መከራ ሲያከትም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተፈጻሚነት ያገኛሉ።”


እዚያም ቆመው ከነበሩት ወደ አንዱ ቀረብ ብዬ የዚህን ሁሉ እውነት ትርጒም ጠየቅሁት፤ እርሱም የዚህን ሁሉ ትርጒም ነገረኝ።


ሎደባር የምትባለውን ከተማ በማሸነፋችሁ ተደስታችኋል፤ “ቃርናይም የምትባለውንም ከተማ በጒልበታችን ይዘናል” ብላችሁ ትፎክራላችሁ።


እኛን ለመበታተን እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጣውን የጦረኞቹን አለቃ በገዛ ቀስቱ ወጋኸው። ደካማ እንስሶችን ለመቦጨቅ እንደሚጓጓ አውሬ እርሱም የተደበቁትን ድኾች ለማጥቃት የተዘጋጀ ነበር።


በሌላም ራእይ አራት የበሬ ቀንዶችን አየሁ፤


እኔም “እነዚህ ሰዎች የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “እነርሱ የመጡት የይሁዳን ምድር ፈጽሞ አጥፍተው፥ ሕዝብዋ ተበታትኖ እንዲቀር ያደረጉትን የአሕዛብ መንግሥታት ለማሸበርና ለመጣል ነው” አለኝ።


እኔም “ጌታዬ ሆይ! እነዚህ ፈረሶች የምን ምሳሌ ናቸው?” ብዬ ጠየቅሁት። እርሱም “የእነዚህ ፈረሶች ምሳሌነት ምን እንደ ሆነ አሳይሃለሁ፤


እኔም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያኽል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።


“እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ባለመራራት ቅጣት ላመጣባችሁ ወሰንኩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos