የሟቹ ሚስት በከተማይቱ መሪዎች ፊት ወደ እርሱ ትቅረብ፤ ከእግሩ ጫማዎች አንዱን አውልቃ ምራቋን በፊቱ ላይ በመትፋት ‘ለወንድሙ ዘር ለመተካት እምቢ ለሚል ሰው ይህን ዐይነት አሳፋሪ ነገር ሊፈጸምበት ይገባል’ ትበል።
ሩት 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰውየው ቦዔዝን “አንተ ልታስቀረው ትችላለህ” ብሎ ጫማውን አውልቆ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅድሚያ ያለው ቅርብ የሥጋ ዘመድም ቦዔዝን፣ “እንግዲህ አንተው ራስህ ግዛው” ብሎ ጫማውን አወለቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ “አንተ ግዛው” አለው፤ ጫማውንም አወለቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ አንተ ግዛው አለው፣ ጫማውንም አወለቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን “አንተ ግዛው” አለው፤ ጫማውንም አወለቀ። |
የሟቹ ሚስት በከተማይቱ መሪዎች ፊት ወደ እርሱ ትቅረብ፤ ከእግሩ ጫማዎች አንዱን አውልቃ ምራቋን በፊቱ ላይ በመትፋት ‘ለወንድሙ ዘር ለመተካት እምቢ ለሚል ሰው ይህን ዐይነት አሳፋሪ ነገር ሊፈጸምበት ይገባል’ ትበል።
በቀድሞ ዘመን በእስራኤላውያን ዘንድ የመግዛትና የመሽጥ፥ እንዲሁም ንብረትን የማስተላለፍ ልማድ እንዲህ ነበር፤ ውሉን ለማጽደቅ አንዱ ወገን ጫማውን አውልቆ ለሌላው ወገን ይሰጥ ነበር፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ውል ለመፈጸሙ ማረጋገጫ ነበር።
ከዚህ በኋላ ቦዔዝ ለሽማግሌዎቹና እዚያ ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! የአቤሜሌክንና የልጆቹን የኬሊዎንና የማሕሎንን ንብረት ሁሉ ዛሬ ከናዖሚ በውርስ እንዳስቀረሁት እናንተ ሁላችሁ ምስክሮች ናችሁ፤