ሩት 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀድሞ ዘመን በእስራኤላውያን ዘንድ የመግዛትና የመሽጥ፥ እንዲሁም ንብረትን የማስተላለፍ ልማድ እንዲህ ነበር፤ ውሉን ለማጽደቅ አንዱ ወገን ጫማውን አውልቆ ለሌላው ወገን ይሰጥ ነበር፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ውል ለመፈጸሙ ማረጋገጫ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥንት ዘመን በእስራኤል የመቤዠትም ሆነ ንብረት የማስተላለፍ ጕዳይ የሚጸናው አንዱ ወገን ጫማውን አውልቆ ለሌላው ወገን ሲሰጠው ነው፤ በእስራኤል ዘንድ መሸጥም ሆነ መግዛት ሕጋዊነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ውል ለመፈጸሙ ማረጋገጫ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤል ምስክር ነበረ። |