ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
ሩት 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚም “እውነት ነው ልጄ፤ በቦዔዝ እርሻ ካሉት ሴቶች ጋር ሆነሽ ብትቃርሚ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ብትሄጂ ግን ምናልባት ጐልማሶች ያስቸግሩሻል” አለቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑኃሚንም ምራቷን ሩትን፣ “የእኔ ልጅ፤ እንዲህ ካልሽማ ከሴት ሠራተኞቹ ጋራ ዐብሮ መሄድ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው አዝመራ ብትሄጂ ጕዳት ሊያገኝሽ ይችላልና” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዖሚም ምራትዋን ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ከሴት አገልጋዮቹ ጋር ብትወጪ ይሻላል፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ምራትዋን ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚኃሚንም ምራትዋን ሩትን “ልጄ ሆይ! ከገረዶቹ ጋር ብትወጪ፥ በሌላም እርሻ ባያገኙሽ መልካም ነው፤” አለቻት። |
ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ያማርሽ ውብ ሆይ! ቦታውን የማታውቂው ከሆነ የበጎቹን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።
ስለዚህ ሩት የገብሱና የስንዴው መከር ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ በቦዔዝ ገረዶች አጠገብ እየቃረመች ቈየች፤ ከዐማትዋም ሳትለይ አብራ ተቀመጠች።