“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤
ሩት 2:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ልትቃርም ስትነሣ ቦዔዝ ጐልማሶቹን እንዲህ አላቸው፦ “በነዶዎች መካከል ያለውንም እንኳ ቢሆን ትቃርም፤ እናንተም አትከልክሉአት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመቃረም ስትነሣም፣ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “በነዶው መካከል እንኳ ብትቃርም ክፉ አትናገሯት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ብላቴኖቹን፦ “በነዶው መካከል ትቃርም፥ እናንተም አትከልክሏት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን፦ በነዶው መካከል ትቃርም፥ እናንተም አታሳፍሩአት፣ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ልትቃርም በተነሣች ጊዜ ቦዔዝ ጐበዛዝቱን “በነዶው መካከል ትቃርም፤ እናንተም አታሳፍሩአት፤ |
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤
“የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር አትጨዱ፤ የመከሩንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤ እርሱን ለድኾችና ለመጻተኞች ተዉላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።
በምሳ ሰዓት ቦዔዝ ሩትን “ነይ ወደ ገበታው ቅረቢ፤ በወጡም እያጠቀስሽ እንጀራ ብዪ” አላት። እርስዋም ከአጫጆቹ ጋር ተቀመጠች፤ ቦዔዝም የተጠበሰ እሸት ሰጣት፤ እስክትጠግብ ድረስ በላች፤ ምግብም ተርፏት ነበር።