ሮሜ 16:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን መልእክት የጻፍኩ እኔም ጠርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን መልእክት የጻፍሁት እኔ ጤርጥዮስ፣ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ቴርትዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህችን መልእክት የጻፍኋት እኔ ጤርጥዮስ በጌታችን ስም ሰላም እላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። |
በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።
እነሆ እኔ ጳውሎስ “ዕዳውን እከፍልሃለሁ” ብዬ በገዛ እጄ ጽፌ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሆኖም ስለ ሕይወትህ አንተ ራስህ እንኳ የእኔ ባለዕዳ መሆንክን እኔ ላስታውስህ አያስፈልግም።