ሮሜ 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቀጣቸውም ስለ እግዚአብሔር ማወቅ የሚገባቸውን እግዚአብሔር ራሱ ገልጦላቸው ያውቁ ስለ ነበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው ለእነርሱ ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእነርሱ ግልጽ አድርጎታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እግዚአብሔር መታወቅ የሚገባው በእነርሱ መካከል ግልፅ ነው፤ ምክንያቱም ለእነርሱ እግዚአብሔር ግልፅ አድርጎላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው እግዚአብሔርን ማወቅ በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። |
ቀና ብላችሁ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፤ የምታዩአቸውን ከዋክብት የፈጠረ ማን ነው? እርሱ እንደ ጦር ሠራዊት ይመራቸዋል፤ ምን ያኽል እንደ ሆኑም ቊጥራቸውን ያውቃል፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል፤ የእርሱ ሥልጣንና ኀይል እጅግ ታላቅ ነው፤ ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይጠፋም።
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለሰዎች የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፥ ይኸውም ዘለዓለማዊው ኀይሉና አምላክነቱ እርሱ በፈጠራቸው ነገሮች አማካይነት ግልጥ ሆኖ ስለ ታየ ሰዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ምክንያት የላቸውም።
ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮአቸው ሕግ የሚያዘውን ነገር ይፈጽማሉ፤ በዚህም ምክንያት ሕግ ባይኖራቸውም የራሳቸው የተፈጥሮ ሕግ ስላላቸው ማድረግ የሚገባቸውን ያውቃሉ።