ከሲኦል ኀይል እታደጋቸዋለሁን? ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ! መቅሠፍቶችህ የት አሉ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ የት አለ? እኔኮ አልራራላቸውም፤
ራእይ 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞትና ሲኦልም ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፤ ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፤ የእሳቱ ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። |
ከሲኦል ኀይል እታደጋቸዋለሁን? ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ! መቅሠፍቶችህ የት አሉ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ የት አለ? እኔኮ አልራራላቸውም፤
የእግዚአብሔርን የቊጣ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቊጣው ጽዋ የተቀዳ ነው፤ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሠቃያሉ፤
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።
ባሕርም በውስጡ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ውስጥ የነበሩትን ሙታን ሰጡ፤ እያንዳንዱም ሰው በሥራው መሠረት ፍርድ ተቀበለ።
የመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ የተመሰገኑና ቅዱሳን ናቸው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ እነርሱ የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”
እነሆ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ይባል ነበር፤ ሲኦልም ይከተለው ነበር፤ ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ እጅ በጦርነት፥ በራብ፥ በቸነፈርና በምድር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።