ራእይ 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ከሚያሠቃየው እሳት የሚወጣው ጢስ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል። ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ ወይም የስሙንም ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሥቃያቸውም ጢስ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፥ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም። |
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።
ቀንና ሌሊት ትቃጠላለች፤ ጢስም ከእርስዋ መውጣቱን ለዘለዓለም አያቋርጥም፤ ምድሪቱም በዘመናት ሁሉ የማትጠቅም ባድማ ትሆናለች፤ ዳግመኛ በእርስዋ ውስጥ አልፎ የሚሄድ አይኖርም።
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍትና ለእግርህ ማሳረፊያ ቦታ አይኖርህም፤ እግዚአብሔርም የባባ ልብ፥ በናፍቆት የፈዘዘ ዐይን፥ ተስፋ የቈረጠ ስሜት ይሰጥሃል።
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።
የመጀመሪያውን አውሬ ተክቶ በእርሱ ሥልጣን ይሠራ ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለመጀመሪያው አውሬው እንዲሰግዱ አደረገ፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያደርስ ቊስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።
ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ምስል የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን ተሰጠው፤ የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠውም ምስሉ ለመናገር እንዲችልና ለእርሱ የማይሰግዱት ሁሉ እንዲገደሉ ያደርግ ዘንድ ነው።
ሌላ ሦስተኛ መልአክም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ፥ ምልክቱን በግንባራቸው ወይም በእጃቸው የሚያደርጉ ሁሉ፥
ያሳታቸው ዲያብሎስ፥ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት በዲን በሚቃጠል እሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ፤ በዚያም ሌሊትና ቀን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሠቃያሉ።
ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።
እንዲህም አሉ፦ “አሜን! ውዳሴ፥ ገናናነት፥ ጥበብ፥ ምስጋና፥ ክብር፥ ኀይል፥ ብርታት ለአምላካችን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።”