በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የአገልጋይህን ቤት ለመባረክ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በበረከትህ እንደ ተናገርክ የአገልጋይህ ቤት ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን።”
መዝሙር 89:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰጠኸውም የተስፋ ቃል “ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለአገልጋዬም ለዳዊት ማልሁ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ሰዓት ነውና። |
በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የአገልጋይህን ቤት ለመባረክ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በበረከትህ እንደ ተናገርክ የአገልጋይህ ቤት ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን።”
ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ።
ለእኔ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ መንግሥቱም በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።’ ”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ይሁዳን በእስራኤል ላይ መሪ ነገድ አድርጎ መርጦታል፤ ከይሁዳም የእኔን ቤተሰብ፥ ከእኔም ቤተሰብ እኔን የእስራኤል ንጉሥ እንድሆን መረጠኝ፤ የእኔም ዘሮች ነገሥታት ሆነው እንደሚያስተዳድሩ ቃል ገብቶልኛል።
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደ ጋሻ መከታ እሆንላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ እጅግ ደካማ የተባለው እንኳ የዳዊትን ያኽል ብርቱ ይሆናል፤ የዳዊት ልጆች እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ወይም እንደ መላእክት ሆነው ሕዝቡን ይመራሉ።
እንዲሁም ኢሳይያስ፦ “ከእሴይ ዘር የሚወለድ ይመጣል፤ የአሕዛብም መሪ ለመሆን ይነሣል፤ እነርሱም ተስፋቸውን በእርሱ ላይ ያደርጋሉ” ይላል።
“እኔ ኢየሱስ ይህን ምስክርነት እንዲሰጣችሁ መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያን ልኬአለሁ፤ እኔ የዳዊት የትውልድ ሐረግና ዘር ነኝ፤ የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነኝ።”