የቤተ መቅደስህን አደባባይ በጣም እናፍቃለሁ፤ ለሕያው አምላክ በሙሉ ልቤ በደስታ እዘምራለሁ።
ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!
የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር አልህ፤ ዐበሳቸውንም ሁሉ ሰወርህ።
የሚገኝበትን ቦታ ባውቅ እንዴት በወደድሁ ነበር፤ ወደሚኖርበትም ቦታ ብደርስ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፤
ነፍሴ ሥርዓትህን ለማግኘት ሁልጊዜ በመናፈቅ ተጨነቀች።
የአንተን አዳኝነት በሙሉ ልቤ እመኛለሁ። እምነቴን በቃልህ ላይ አድርጌአለሁ።
እጆቼን ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤ ደረቅ ምድር ውሃ እንደሚያስፈልገው እንዲሁም ነፍሴ አንተን ተጠማች።
አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ እኔ ከፍቅሩ የተነሣ መታመሜን እንድትነግሩት ዐደራ እላችኋለሁ።
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
ምነው ሰማያትን ከፍተህ ብትወርድ፤ ተራራዎችም አንተን አይተው ምነው በተንቀጠቀጡ፤
ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ፥ የሰፈርክባቸው ቦታዎች ምንኛ ያምራሉ?