የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤ ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
የእስረኞች ሰቈቃ በፊትህ ይድረስ፤ በክንድህም ብርታት፣ ሞት የተፈረደባቸውን አድን።
የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፥ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።
ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
ይህንንም ያደረገው የእስረኞችን መቃተት ሰምቶ ሞት የተፈረደባቸውንም ነጻ ለማውጣት ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን ይነገራል፤ በኢየሩሳሌምም ይመሰገናል።
እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።
እግዚአብሔር የችግረኞችን ጩኸት ይሰማል፤ በእስር ቤት ያሉትን ወገኖቹንም ችላ አይላቸውም።
አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ እናደርጋለንና ማረን! ማረን! በየቀኑ ጥበቃህ አይለየን፤ በመከራ ጊዜም ታደገን።
ስለዚህ የዕውሮችን ዐይን ታበራለህ፤ በጨለማው ጒድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያሉትን እስረኞችን ታወጣለህ።
ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]
ስለዚህ በእኛ ውስጥ በሚሠራው ኀይሉ አማካይነት ከምንለምነውና ከምናስበው በላይ እጅግ አትረፍርፎ ሊያደርግ ለሚቻለው አምላክ፥