በዚህ ዐይነት ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ምግብ ሁሉ ሰጣቸው።
ሰዎች የኀያላንን እንጀራ በሉ፤ ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው።
የመላክትንም እንጀራ ሰው በላ ስንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው።
ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤ እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
ምግብ በጠየቁት ጊዜ ድርጭቶችን ላከላቸው። ከሰማይ እንጀራን ልኮ አጠገባቸው።
ከዚህም በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፦ “በእርሱ ላይ ማጒረምረማችሁን ስለ ሰማ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የፈለጋችሁትን ያኽል እንጀራ የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው፤ እኛ ምንድን ነን? በእኛ ላይ ስታጒረመርሙ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረማችሁ ነው።”
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውን ፍርፋሪ፥ ደቀ መዛሙርቱ በዐሥራ ሁለት መሶብ ሞልተው አነሡ።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ደቀ መዛሙርቱ ሰብስበው ሰባት መሶብ ሙሉ ፍርፋሪ አነሡ።