ለድኾችና ለደካሞች ይራራል፤ በችግር ላይ ያሉትንም ሰዎች ከሞት ያድናል።
ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ድኾችንም ከሞት ያድናል።
ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።
እንዲህም አልሁ፥ “በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁአትን?” እጆቼንም በንጽሕና አጠብሁ።
ምክንያቱም እርሱ ሊገድሉት ከተዘጋጁ ሰዎች እጅ ሊያድነው ስለ ድኻ ሰው መብት ይከራከራል፤
“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው ዘወትር በሰማይ ያለውን ያባቴን ፊት ስለሚያዩ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ። [
“መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ስለ ሆነች በመንፈሳዊ ኑሮአቸው ድኾች መሆናቸው የሚሰማቸው የተባረኩ ናቸው።