ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
መዝሙር 69:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤትህ ያለኝ ቅናት በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በአንተ ላይ የተሰነዘረው ስድብ በእኔ ላይ ዐረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤትህ ቅናት በላችኝ፤ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው። |
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ከእነዚህ ካዘጋጀኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካለኝ ታላቅ ፍቅር የተነሣ ከራሴ ንብረት ብዙ ብርና ወርቅ ሰጥቼአለሁ፤