ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።
መዝሙር 68:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! የድል አድራጊነትህ ሰልፍ በሁሉም ይታያል፤ የእኔ ንጉሥና አምላክ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ ሲገባ ይታያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ የክብር አካሄድህ ታየ፤ ይህም አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገው የክብር አካሄድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው። |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።