የግጦሽ ስፍራዎች በመንጋ የተሞሉ ይሆናሉ፤ ተራራዎችም ደስታን እንደ ልብስ ይለብሳሉ።
የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ፈለጎችህ ስብን ይጠግባሉ።
በራሳችን ላይ ሰውን አስጫንህ፤ በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
በኀይልህ ተራራዎችን አጽንተሃል፤ ብርታትንም ታጥቀሃል።
እናንተም የምድር እንስሶች አትፍሩ፤ የምትሰማሩባቸው መስኮች ለምልመዋል፤ ዛፎችም አፍርተዋል፤ የበለሱና የወይኑ ፍሬ እጅግ የበዛ ሆኖአል።