ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትሰጣለህ፤ ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ፤ ዐፈሩንም በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ።
ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ ቦይዋን ታስተካክላለህ፤ በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፥ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፥ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥ ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና።
እግዚአብሔር ዝናብን የሚያዘንበው፥ ምድርን ለማረስረስ፥ ሰዎችን ለመቅጣት፥ ወይም ፍቅሩን ለመግለጥ ነው።
ከሰማይ ዝናብን በተራሮች ላይ ታወርዳለህ፤ ምድርም በምትሰጣት በረከት ትሞላለች።
እርሱ ደመናን በሰማይ ላይ ይዘረጋል፤ ለምድር ዝናብን ይሰጣል፤ ተራራዎችንም በለምለም ሣር ይሸፍናል።
ሕዝቦችህም መኖሪያቸውን በዚያ አደረጉ፤ በቸርነትህም ለድኾች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አዘጋጀህላቸው።
ምድራችሁ በሰብል፥ ዛፎቻችሁም በፍሬ የተሞሉ ይሆኑ ዘንድ ዝናብን በወቅቱ እልክላችኋለሁ።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥