ነገር ግን ቈይቼ ብመለስ ከስፍራው አጣሁት፤ ብፈልገውም ላገኘው አልቻልኩም።
ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ ብፈልገውም አልተገኘም።
ብመለስ ግን አጣሁት፥ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።
አንድ ሰው ከቦታው ቢነቅለው የነበረበት ቦታ አይታወቅም።
ክፉዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፤ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉ አድራጊዎች ፈጥነው ይጠፋሉ፤ ብትፈልጋቸው እንኳ አታገኛቸውም።
“እስራኤላውያን በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻገሩ፤ የፈርዖን ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞቹ ሁሉ ወደ ባሕር በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ውሃውን መለሰባቸው።”
ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።
በምሽት ጊዜ እነሆ፥ ሽብር ይሆናል፤ በማለዳ ግን ይጠፋሉ፤ የሚዘርፉንና የሚበዘብዙን ሰዎችም ዕድል ፈንታ ይኸው ነው።
መጨረሻሽ አስፈሪ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍጻሜሽ ይሆናል፤ ሰዎች ቢፈልጉሽ እንኳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቶ አያገኙሽም፤” እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።