ከአታላዮች ጋር አልወዳጅም፤ ከግብዞችም ጋር አልተባበርም፤
ከማይረቡ ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከግብዞችም ጋራ አልተባበርሁም።
ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥ ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም።
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ።
“ሐሰት ተናግሬ እንደ ሆነ፥ ሰውንም አታልዬ እንደ ሆነ፥
በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።
ጠማማ ልብ ያላቸው ሰዎች ከእኔ ይራቁ፤ ከክፋትም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም።
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ፤ እኔ የአምላኬን ትእዛዞች መጠበቅ እፈልጋለሁ።
አንተን የሚፈሩትንና ሕግህን የሚያከብሩትን ሁሉ እወዳቸዋለሁ።
ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤ በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።
ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።
ዕውቀት ከጐደላቸው ሰዎች ተለይ! በሕይወትም ትኖራለህ፤ በማስተዋልም መንገድ ወደፊት ተራመድ።”
ከሚፈነጥዙ ሰዎች ጋር አልተወዳጀሁም፤ ከእነርሱም ጋር አልተደሰትኩም፤ ቊጣህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ብቻዬን ተቀመጥኩ።
አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”
ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎአል፦ “ከእነርሱ መካከል ተለይታችሁ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤