አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
መዝሙር 25:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፈለግህንም አስተምረኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዐመፀኞችም ጋር አልገባሁም። |
አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
የምተማመነው በአንተ ስለ ሆነ በየጠዋቱ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ ሕይወቴን በዐደራ ለአንተ ስለ ሰጠሁ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።
አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ እንዳገለግልህና አንተን በማስደሰት እንድቀጥል እባክህ መንገድህን አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት።”
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።