መዝሙር 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ ቢያቅዱና ቢያድሙም ምንም አይሳካላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ። |
ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።
እንዲህ ብሎም ወደ ቤተልሔም ላካቸው፦ “ሂዱና፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ፥ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ።”