La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤ ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘራቸውን ከምድር፣ ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥ ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ልሁ፤ ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀም​ረህ አንተ አም​ላኬ ነህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 21:10
8 Referencias Cruzadas  

እነርሱን ለመዳሰስ የብረት ልብስ ወይም የጦር ዛቢያ ያስፈልጋል፤ በዚያን ጊዜ ባሉበት ፈጽመው ይቃጠላሉ።


ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ።


በእግዚአብሔርም የቊጣ ቀን የቤቱ ንብረት ሁሉ በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።


ለስሙ መጠሪያ የሚሆን አንድ ልጅ እንኳ አይቅርለት፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚያስታውሰው አይኑር።


እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


አንተ አገርህን አጥፍተህ፥ የገዛ ሕዝብህን ፈጅተሃል፤ ስለዚህም አንተ እንደ ሌሎች መንግሥታት መቃብር የማግኘት ዕድል አይኖርህም፤ ከክፉ ቤተሰብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖርም።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።