ዳዊትም ወሬውን ይዞ የመጣውን ያንን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “በሀገርህ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር የዐማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።
መዝሙር 18:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። |
ዳዊትም ወሬውን ይዞ የመጣውን ያንን ወጣት “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “በሀገርህ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር የዐማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።
በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።
እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።
ስብንና ደምን ለእኔ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑትን ያልተገረዙ ባዕዳን ወደ ተቀደሰው ስፍራዬ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አርክሳችኋል፥ በረከሰውም ተግባራችሁ ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋል።
እስራኤል ሆይ! የእርዳታህ ጋሻ፥ የድልህ ሰይፍ መዳንን ከእግዚአብሔር ያገኘ፥ እንዳንተ ያለ ሕዝብ ከቶ የለም፤ ምንኛ የታደልክ ነህ! ጠላቶች እየተለማመጡ ወደ አንተ ሲመጡ ጀርባቸውን ትረግጣለህ።