ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ በገና እየደረደራችሁ ለአምላካችን ዘምሩ።
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
የዓለም መንግሥታት ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።
በገና በመደርደርና በመዘመር ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ!