ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥ በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ።
ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዷቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ።
መሄድስ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፥ መመለስስ፥ ነዶአቸውን ተሸክመው በእልልታ ይመጣሉ።
እርሱ የሚቈጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን ለዘለዓለም ነው፤ ሌሊት ሲለቀስ ዐድሮ በማለዳ ደስታ ይሆናል።
ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ “ከቶ አልሸነፍም” አልኩ።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።