የምወዳቸውን ትእዛዞችህን አከብራለሁ፤ ስለ ሥርዓትህም በተመስጦ አሰላስላለሁ።
እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።
እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፥ ሥርዓትህንም አሰላስላለሁ።
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
እንዲህ ያለው ሰው፥ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፤ ቀንና ሌሊትም ያሰላስለዋል።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ተነሥ! አምላክ ሆይ፥ ኀያል ክንድህን አንሣ! የተጨቈኑትንም ችላ አትበላቸው።
ሥርዓትህን አጠናለሁ፤ በምትመራኝ መንገድ ላይም አተኲራለሁ።
ሕግህን እጅግ እወዳለሁ፤ ስለ እርሱ ቀኑን ሙሉ አስባለሁ።
ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው የጣዖት አምልኮ ሥርዓት መሪዎች በመሆን ሕዝቡን ወደ ኃጢአት ስለ መሩ መቀጣት እንደሚገባቸው በራሴ ምዬአለሁ” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
የእስራኤል ኀይል በጠላቶቹ ላይ ይነሣል፤ ጠላቶቹም ሁሉ ይጠፋሉ።
‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፤ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ነው።
ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ።
እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።