La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 109:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰውየው ደግ ሥራ ለማድረግ ፈጽሞ አላሰበም፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና ምስኪኖችን እያሳደደ ይገድል ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በቸርነት ለመመላለስ አላሰበምና፥ ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ለመግደል ያሳድድ ነበር።

Ver Capítulo



መዝሙር 109:16
16 Referencias Cruzadas  

እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።


ክፉ ሰዎች ይታበያሉ፤ ድኾችንም ያሳድዳሉ፤ ለሌሎች በዘረጉት ወጥመድ ራሳቸው ይጠመዱ።


ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።


ክፉዎች፥ ድኾችንና ምስኪኖችን ለመግደል፥ ደግ ሥራ የሚሠሩትንም ለማረድ፥ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ቀስታቸውን ያዘጋጃሉ።


ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል።


ምሕረትን ስለሚያገኙ ምሕረትን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።