ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
መዝሙር 106:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥ እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና። |
ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።