በዚያ ሳሉ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮችና፥ በቀይ ባሕርም ያደረገላቸውን አስገራሚ ነገሮች ዘነጉ።
እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ።
የምስጋና መሥዋዕትም ይሠዉለት፥ በደስታም ሥራውን ይንገሩ።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ በዚያም አገር ስደተኛ ሆኖ ኖረ።
የካምን ልጆች የመጀመሪያ የወንድነት ፍሬ፥ በግብጽ በኲሮችን ሁሉ ገደለ።
ነገር ግን አምላክ ሆይ፥ ከአንተ በተገኘው በአንድ ትንፋሽ ግብጻውያን ሁሉ ሰጠሙ፤ በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደ ተጣለ ብረት ሆነው ቀሩ።