የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ።
ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ።
ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።
ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።
ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል።
እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።
ሐሰተኞች አማልክት ቢሆኑም እንኳ አማልክቱን የሚቀያይር ሕዝብ የለም፤ ሕዝቤ ግን ክብር ያጐናጸፍኳቸውን እኔን አምላካቸውን ምንም ሊያደርጉላቸው በማይችሉ ከንቱ አማልክት ለውጠውኛል።”