በንጉሡ ባለሥልጣኖች ላይ አዛዥ ሆነ፤ ለንጉሡም አማካሪዎች ጥበብን ያስተምራቸው ዘንድ ሥልጣን ተሰጠው።
ይኸውም ሹማምቱን በራሱ መንገድ ይመራ ዘንድ፣ ሽማግሌዎቹንም ጥበብ ያስተምር ዘንድ ነበር።
መኰንኖቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
ድንቅንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን።
“እንግዲህ ጥበብና ማስተዋል ያለውን ሰው መርጠህ በአገሪቱ አስተዳዳሪ አድርገህ ሹመው፤
ንጉሡም “የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረበት ከዮሴፍ የተሻለ ሰው ከቶ አናገኝም” አላቸው።
ንጉሡም “እኔ ንጉሥ ብሆንም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው።
በጾዓን ያሉ የንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ጠቢባን የሆኑት የግብጽ ንጉሥ አማካሪዎች ጥቅም የሌለው ምክር ይመክራሉ፤ እንዴት አድርገው ለንጉሡ “እኛ ብልኆች ነን፤ ዘራችንም ከቀድሞ ነገሥታት ሲወርድ፥ ሲዋረድ የመጣ ነው” ይላሉ?