እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
መዝሙር 104:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስ መልእክተኛህ ነው፤ የእሳት ነበልባልም አገልጋይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፋሳትን መልእክተኞቹ የሚያደርግ፥ የእሳት ነበልባልም አገልጋዮቹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፤ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። |
እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!” ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕ አገልጋይ ዐይኖቹ እንዲከፈቱለት ስላደረገ፥ በኰረብታው ጐን ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተሰልፈው የሚጠብቁት መሆናቸውን ተመለከተ።
በሕያዋን ፍጥረቶቹ መካከል እንደሚነድ ከሰል እሳት የሚመስል ነገር ነበር፤ እርሱም በፍጥረቶቹ መካከል ወዲያና ወዲህ የሚንቀሳቀስ ችቦ ይመስል ነበር፤ እሳቱ ብሩህ ነበር፤ መብረቅም ከዚያ ይወጣ ነበር።