የሕይወት ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ በማለቅ ላይ ነው፤ ሰውነቴም እንደ እሳት እየነደደ ነው።
ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።
ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
ቆዳዬ ጠቊሮ ተገለፈፈ፤ ሰውነቴም በትኩሳት ተቃጠለ።
ጢስ በሚጤስበት ቤት ተሰቅሎ እንደ ተጨማደደ የወይን ጠጅ አቊማዳ ከጥቅም ውጪ ሆኜአለሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ሕግህን አልረሳሁም።
አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ።
ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ በረሓ አበባ ይረግፋሉ፤ እንደ ጢስም ከዓይን ይሰወራሉ።
ከቊጣህ የተነሣ ሥጋዬ ደኅንነት የለውም። በኃጢአቴም ምክንያት መላ ሰውነቴ ጤንነት የለውም።
“ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ።
ሥጋዬንና ቆዳዬን አስረጀ፤ አጥንቶቼንም ሰባበረ።
ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ።