እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
መዝሙር 102:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ እነርሱ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ፤ ይወገዱማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። |
እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።
ቀና ብላችሁ ወደ ሰማያት ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በነው ይጠፋሉ፤ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤ በእርስዋ የሚኖሩ ሁሉ እንደ ዝንብ ይሞታሉ፤ የእኔ ማዳን ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ ለታዳጊነቴም ፍጻሜ የለውም።
ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያይቱ ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።