ምሳሌ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቢብን አስተምረው፥ በይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ደግን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀትን ይጨምራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ይበልጡን ጠቢብ ይሆናል፥ ጻድቅንም አስተምረው፥ ይበልጡን አዋቂ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል። |
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።