ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።
ምሳሌ 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላዘጋጀችውም ግብዣ ፍሪዳ ዐረደች፤ የጣፈጠ የወይን ጠጅም ጠመቀች፤ ገበታም ዘርግታ ማእድ ሠራች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍሪዳዋን ዐረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ ማእዷንም አዘጋጀች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን አዘጋጀች፥ ማዕድዋን አሰናዳች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች። ማዕድዋን አዘጋጀች። |
ዮሴፍ ብንያምን ከእነርሱ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ ጠራውና “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ ዛሬ ቀን ከእኔ ጋር ምሳ ስለሚበሉ አንድ ከብት ዕረድና አዘጋጅ” አለው።
ወደ ወላጅ እናቴ ቤት ባስገባሁህ ነበር፤ በዚያም ስለ ፍቅር ባስተማርከኝ ነበር፤ በሮማን ፍሬዬ ጭማቂ የጣፈጠውን መልካሙን የወይን ጠጅ ባጠጣሁህ ነበር።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።