ምሳሌ 9:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ አማካይነት ዕድሜህ ይረዝማል፤ ለሕይወትህም ዓመቶች ይጨመራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘመንህ በእኔ ምክንያት ይረዝማልና፤ ዕድሜም በሕይወትህ ላይ ይጨመርልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥ የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል። |
ይህን ብታደርግ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል በገባላቸው ምድር የአንተና የልጆችህ ዘመን ከምድር በላይ እንዳለው ሰማይ ይረዝማል።
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ።
በዚያች ምድር ለረጅም ዘመናት መኖር እንድትችሉ አንተና ልጆችህ፥ የልጅ ልጆችህም በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትና እኔ ለሰጠኋችሁ ደንቦችና ትእዛዞች ታዛዦች መሆን ይገባችኋል።