ምሳሌ 8:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባሕር ውሃዎች ከተመደበላቸው ስፍራ በላይ ከፍ እንዳይሉ ባዘዛቸው ጊዜ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ እኔ እዚያ አብሬው ነበርኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ ውሆችም የርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣ የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት በመሠረተ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥ |
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።