ምሳሌ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገባኸውም ቃል ብትያዝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣ ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥ በአፍህ ቃል ከተያዝህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ከንፈሩ ጽኑ ወጥመድ ነው፤ በአፉ ቃል ይጠፋል። |
ልጄ ሆይ! በዚያ ሰው ሥልጣን ሥር ሆነሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእርሱ ቊጥጥር ነጻ ለመውጣት ብትፈልግ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ ዋስትናውንም እንዲያወርድልህ ለምነው።
ጣዖቶቻቸውን በእሳት አቃጥል፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ የራስህ ንብረት አድርገህ ለመውሰድ ልብህ አይመኝ፤ ይህን ብታደርግ ወጥመድ ይሆንብሃል፤ እግዚአብሔርም አምልኮ ጣዖትን ስለሚጠላ ብርቱ ጥፋትን ያስከትልብሃል።