ምሳሌ 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንገዶችዋ ወደ ሞት የሚያደርሱ ናቸው፤ እርምጃዎችዋም ወደ ሲኦል ይመራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮችዋም ወደ ስንፍና ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሞትና ወደ ሲኦል ያደርሳል። ፍለጋዋ ከኀጢአት ቦታ አይርቅም፥ |
ከሞት ይልቅ የመረረ ሌላም ነገር አገኘሁ፤ ይኸውም የሴት ወጥመድነት ነው፤ ሴት እንደ መረብ በሆነ ፍቅርዋ ወንዶችን ታጠምዳለች፤ እንደ እግር ብረት በሆኑ ክንዶችዋም ተጠምጥማ ለመያዝ ትፈልጋለች፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ብቻ ከእርስዋ ሸሽቶ ማምለጥ ይችላል፤ ኃጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
እነሆ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ይባል ነበር፤ ሲኦልም ይከተለው ነበር፤ ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ እጅ በጦርነት፥ በራብ፥ በቸነፈርና በምድር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።