ሀብትህን ሁሉ ባዕዳን ሰዎች ይወስዱታል፤ የደከምክበትም ንብረት ለሌላ ሰው ይሆናል።
ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።
ሌሎች ከኃይልህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም ወደ ባዕድ ሰው ቤት እንዳይሄድ።
ባዕዳን በሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ የድካምህም ፍሬ በባዕድ ሰው ቤት እንዳይገባ።
ጥበብን የሚወድ አባቱ ያስደስታል፤ አመንዝሮችን የሚከተል ግን ሀብቱን ያባክናል።
ጒልበትህን በዝሙት አትጨርስ፤ ይህ ድርጊት ነገሥታትን ሳይቀር አዋርዷል።
ሁለንተናህ ተበልቶ ከማለቁ የተነሣ በሞት ጣዕር ተይዘሃል፥
አለበለዚያ፥ አንተ የነበረህን ክብር ሌሎች ይወስዱታል፤ ገና በወጣትነትህ በጨካኞች ሰዎች እጅ ትገደላለህ፤
አንድ ወንድ ሴትኛ ዐዳሪዋን በአንድ እንጀራ ዋጋ ሊያገኛት ይችላል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ማመንዘር ግን የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል።
ምንም ዐይነት ካሳ መቀበል አይፈልግም፤ የስጦታም ብዛት ቊጣውን አያበርድለትም።
ባዕዳን ጒልበታቸውን በዘበዙት፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም፤ ሽበት ጣል ጣል አድርጎባቸዋል፤ እነርሱ ግን አልተገነዘቡትም።
ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’