ምሳሌ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ ስትሮጥም አትደናቀፍም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥ ብትሮጥም አትሰናከልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም። |
እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።”
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።