ምሳሌ 29:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ ሰው የቊጣ ስሜቱን ይገልጣል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ቊጣውን በትዕግሥት ይገታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ሰው ቍጣውን ያለ ገደብ ይለቅቀዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞኝ ሰው ቁጣውን ሁሉያለችግር ያወጣል፥ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል። |
በሰው ላይ እምነትህን አትጣል፤ በቅርብ ወዳጅህም አትተማመን፤ አቅፈሃት ለምትተኛው ሚስትህ የምትናገረው ቃል እንኳ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።
በመጨረሻ እውነቱን ነገራት፤ እንዲህም አላት፦ “ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆነ ጠጒሬ ተላጭቶ አያውቅም፤ ጠጒሬ ቢላጭ ግን ኀይል ተለይቶኝ እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ።”